በዩናይትድ ኪንግደም ላሉ የጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች የተዘጋጀ ጤና ተኮር መረጃ

ከዚህ ስር NHSን በተመለከተ እንዴት GP ጋር መመዝገብ እንደሚቻል፣ ጤና ጥበቃን በተመለከተ ያሎትን መብት፣ ከሐኪሞች ጋር እንዴት መግባባት እንዳለቦት እንዲሁም እራሶን ጤነኛ እና ወጣት አድርገው ስለሚቆዩባቸው መንገዶች የሚገልፁ ዝርዝር መረጃዎችን  በአማርኛ እና በተወሰነ እንግሊዝኛ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ሥነ ተዋልዶን፣ የልጆችን ጤና፣ የወሊድ ፍቃድ እና የልጅ አስተዳደግን በተመለከተም ጠቃሚ መረጃዎችን ይዟል፡፡  

እዚህ ገፅ ላይ የሚፈልጉትን ካላገኙ እባክዎን ይህንን አሳይለም ዌልካምን ያነጋግሩ፡፡ 

ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች ኤንኤቼስን በምን መልኩ መጠቀም ይችላሉ

የኤንኤቺስን የተለያዩ አገልግሎቶች፣ እንዴት እና መቼ ማግኘት እንደሚቻል የሚያብራራ አጭር ቪድዩ ከላይ በማስፈንጠሪያው አለልዎት፡፡ ቪድዮው ወደ ዩኬ አዲስ የመጡ ሰዎችን፣ በተለይም ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞችን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ቪድዮዉን በአማርኛ ሰብታይትል ለመመልከት መተግበሪያ(setting) ውስጥ በመሄድ አማርኛ የሚለውን ይምረጡ፡፡

የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ወይም ኤንኤችኤስ 

ኤንኤቼስን በተመለከተ 4 ገፅ ሊፍሌት በአማርኛ ተዘጋጅትዎሎታል 

ማንኛውም በእንግሊዝ ውስጥ የሚኖር ሰው የጠቅላላ ሐኪም (GP) ጋር ተመዝግቦ ሕክምና ማግኘት ይችላል፡፡ ለዚህ የመኖሪያ አድራሻዎን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አይጠበቅብዎትም፡፡

ሕክምና የማግኘት መብት እንዳልዎ ስለሚያረጋግጡበት መንገድ

ማን ሕክምናን የማግኘት መብት እንዳለው እና አናክምዎም ቢባሉ ማድረግ ያለብዎትን ነገር የሚገልፅ የአማርኛ መግለጫ(ሰብ ታይትል) ያለው ቪድዮ:

በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ሕክምናን በተመለከተ ያልዎት መብት

GP (ዶክተር) ጋር መመዝገብ ካቃትዎ ከነዚህ ጋርዶች መካከል አንደኛውን ፕሪንት አድርገው ይዘው ይሂዱ:

የጤና ካርድ ስለማግኘት 

ዲጂታል የሕክምና ካርድ ስለማግኘት 

ስለልጆች ጤናማ አኗኗር 4 ገፅ ሊፍሌት:

ጤናማ አኗኗር

የወሲብ እና የሥነተዋልድዎ ጤንነቶን በተመለከተ ማድረግ ስላለብዎት ነገር የሚያሳይ 4 ገፅ የአማርኛ መረጃ:

የወሲብ እና የመራቢያ ጤና

ልጅዎ የጤና እክል ቢገጥመው እጅግ ያስጨንቃል፡፡ ይሄ ድህረ ገፅ (NHS Oxfordshire Healthier Together) የተለመዱ የልጆች ህመሞችን በተመለከተ እና እንዴት የታመመ ልጅን መንከባከብ እንደሚቻል የሚያሳይ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎች አሉት፡፡ በአማርኛ መረጃ ለማግኘት የገፁ እግርጌ በመሄድ የጎግል መተርጎሚያው ላይ በመሄድ የአማርኛ ቋንቋን ይምረጡ።

በዩኬ ውስጥ የእናቶች አገልግሎት የሚሰጠው በአዋላጅ ሐኪሞች ነው፡፡ ማንኛዋም ነብሰ ጡር ሴት በእርግዝናዋ ወቅት እንክብካቤ የሚያደርግላት ወሊዱዋንና ከወለደች በኋላ ያሉትን ጥቂት ቀናት የሚከታተልላት አንድ አዋላጅ ሐኪም ይኖራታል፡፡ አዋላጅ ሐኪሟ አብዛኛው የሚያስፈልግሽን የጤና እንክብካቤ የምታቀርብልሽ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች የጤና ባለሙያዎችን ወይም ዶክተር እንድታዪ ታመቻቻለች፡፡

የእርግዝናን ደህንነት መጠበቅን በተመለከተ አንዳንድ ቡክሌቶች እና ቪድዎች በአማርኛ ተዘጋጅትዎሎታል፡

የእርግዝና ደህንነት መረጃ

የጡት አጠባብ መመሪያ በእንግሊዘኛ

በጡጦ እቃ እንዴት ማጥባት እንዳለብዎ የሚያሳይ መመሪያ (በእንግሊዘኛ)

በእርግዝና ወቅት ለመግባባት የሚያግዝዎት ግብዓቶች:

ክትትል የሚያደርጉልዎ አዋላጅ ሐኪምዎ እና ዶክተርዎ ስለፍላጎትዎ ያዋይዎታል፡፡   የግል ክትትል እቅድ በማውጣት ፍላጎትዎን ሊያሳውቋቸው ይችላሉ፡

የግል የጤና ክትትል እቅድ ለእናቶች እና ቤተሰቦች

ከሌላ የዩንይትድ ኪንግድም ክፍል ወደዚህ ከመጡ፣ አዲሶቹ ሐኪሞችዎ ያሉትን የሕክምና መረጃ ተመለሰው መመልከት እንዲችሉ በእንግሊዘኛ እና አማረኛ የተዘጋጀውን ጋርድ ይጠቀሙ/ያሳዩ፡

ተንቀሳቃሽ የወሊድ ካርድ